በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በአሰላ ቅ/ጽ/ቤት ጎፈር እርሻ ካምፕ ዙሪያ የሚገኝ የቁም ባህርዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ISFO/DA-01/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ በአሰላ ቅ/ጽ/ቤት ጎፈር እርሻ ካምፕ ዙሪያ የሚገኝ የቁም ባህርዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም
- የማንዲላ፣ የአጣና፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ከድርጅቱ ጽ/ቤት አሰላ፣ ባሌ ሮቤ፣ ነቀምቴ እና አዲስ አበባ ጎተራ ተሻለ ጋራዥ ባለኬር ህንጻ ቢሮ ቁጥር 403 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛ የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤት አሰላ፣ ባሌ ሮቤ፣ ነቀምቴ እና በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 331 39 00/29 47 አሰላ ወይም 011 467 38 62 አዲስ አበባ ወይም 022 244 00 11/85 ባሌ ሮቤ ወይም 057 660 37 97 ነቀምቴ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
