በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በአገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ለከተማ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት በጉራጌ ዞን አገና ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በአገና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በአገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ለከተማ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም
ሎት 1. የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
ሎት 2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 3. ሞተር ሣይክል
ሎት 4. የተለያዩ ፈርኒቸር
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ፣ የዘመኑን ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ እና በአንላይ የተመዘገባችሁ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።
- የቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በዘርፉ የጥራት ብቃት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት1 ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ለሎት2 ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) ለሎት3 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለሎት4 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ ቢድ ቦንድ በአገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች ቅድሚያ ሳምፕል ማቅረብ፤ ተጫራቾች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ውል መግባት አለባቸው ያሸነፉት እቃ አገና ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በአንድ ጊዜ አጠቃለው መጋዘን ጥራታቸውን አስፈትሸው ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክሜንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህንን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናት ሳይጨምር አየር ላይ ይውላል። ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ቫት 7.5% ለአገና ከተማ መስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ (መቁረጥ) አለባችሁ።
ማሳሰቢያ፡- ከተማው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-21-61-13-71/09-23-70-27-84/09-35-12-73-41/09-12-47-37-68
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት በጉራጌ ዞን አገና ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
