የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለሳውላ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን
የቤት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ለሳውላ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የሚከራየው ቤት ሙሉ ግቢ ሆኖ ለመዝገብ ቤት የሚሆን አንድ ሰፋ ያለ ክፍል (ስፋቱ ቢያንስ 6×4 ሜትር) የሆነና ሌሎች ተጨማሪ 8 ያህል ለቢሮ አመቺ የሆኑ ስፋታቸው ከ3×4 ያላነሱ ከፍሎች ያሉት መሆን ይኖርበታል፡፡
- የኪራዩ ጊዜ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሶስት ዓመት የሚቆይ ይሆናል።
- የክፍያው ሁኔታ በሁለታችን ስምምነት መሠረት በየ6 ወሩ ወይም በዓመት አንድ ጊዜ በቅድሚያ ከፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የማስረጃው ኮፒ አብሮ መቅረብ ያለበት ሲሆን፣ የሚሰጡትም ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልጽ ማመልከት አለባቸው፤ ካልተገለጸ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡
- ቤቱ ህጋዊና የመንግስት ግብር እየተከፈለበት ያለ ስለመሆኑ ማስረጃ ያለውና የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫው ኮፒ ሆኖ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በሳውላ ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመግዛት የሚያከራዩበትን የአንድ ወር ዋጋ በመሙላትና በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ውጤት በሪጅን ጽ/ቤት (ሀዋሳ) በኩል ተከፍቶና ተወስኖ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ።
አድራሻ፡- ሪጅን ጽ/ቤት (ሀዋሳ) ስልክ ቁጥር 0462214317 ወይም 0462214140 ሳውላ ቅ/ጽ/ቤት መገናኛ ቀበሌ ገዳም ሰፈር አካባቢ
ስልክ ቁጥር 0467771883/0467771972
በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት
