Tender Detail


የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፤ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ ፋክስ ማሽኖች፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፤ ካውንተር እና ኬጂዎች፣ አሉሚኒየም እና ብረታ ብረቶች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ሬሚታንስ ሎጎ ማስታወቂያዎች ፣ ካዝናዎች ፣ የጄኔሬተር ቤቶች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ቆርቆሮዎች እና ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ከጋራጅ ተመላሽ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመሳስሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር FA-01/2025/26)

 

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፤ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ ፋክስ ማሽኖች፣ የቢሮ ወንበር እና ጠረጴዛዎች፤ ካውንተር እና ኬጂዎች፣ አሉሚኒየም እና ብረታ ብረቶች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ሬሚታንስ ሎጎ ማስታወቂያዎች ፣ ካዝናዎች ፣ የጄኔሬተር ቤቶች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ቆርቆሮዎች እና ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ከጋራጅ ተመላሽ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመሳስሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200 (ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊት ለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ሱሉልታ ቻይና ገራጅ በመባል የሚታወቅ አካባቢ ሰላሌ ወተት ማቀነባበርያ ጊቢ ውስጥ ከዋናዉ መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት የሃምሌ 25፣ 29 እና ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ነሃሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ።
  3. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ነሃሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
  4. የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባችኋል በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባቸዋል። ካልሆነ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ባንኩ ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  7. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት አሽናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ውርስ ይደረጋል፡፡
  8. ጨረታው ሰኞ ነሃሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
  9. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር 0115576174

ፖ.ሣ.ቁ 16936

 

ማህበረሰብን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!

 

Save Tender