Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ የተለያዩ የቢሮ ጽሁፍ መገልገያዎችን፤ የጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን፤ የፋብሪካ ዎርክ ሾፕ መገልገያ ዕቃዎችን ኤሌክትሮድ፤ የብየዳ ፤ መነጽር ፤ ጓንት ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)


 

ጨረታ ቁጥር 03/2018

 

ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ የተለያዩ የቢሮ ጽሁፍ መገልገያዎችን፤ የጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን፤ የፋብሪካ ዎርክ ሾፕ መገልገያ ዕቃዎችን ኤሌክትሮድ፤ የብየዳ ፤ መነጽር ፤ ጓንት ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የታደሠ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ በሚመለከተው መ/ቤት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ወይም በመንግስት የአቅራቢነት ዝርዝር ኤሌክትሮኒክ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
  4. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው የቴክኒካል ፖስታ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 03 87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ

 

Save Tender