Tender Detail

Tender Details

  • Company የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቡታጅራ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-145-67-77
  • Website
  • Deadline11 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security30000.00
  • opening date2025-08-11 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

 

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች:-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የTIN NO. ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ ያላቸው እና Online የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ለግዥው ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከሚያቀርቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ ቴክኒካል መረጃዎችን በአንድ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ04፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 04፡30 ሰዓት ላይ ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ፡፡
  6. ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል ፡፡
  8. ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የግዥ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግ/ንብ/አስተ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው መግዛት ይችላሉ ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-145-67-77 ወይም 046-115-06-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ቡታጅራ

 

Save Tender