Tender Detail

Tender Details


በየካ/ከ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ መጻህፍት ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ሞንታርቦ ፣ ዲኮር ፣ ድንኳን ፣ የጭነት አይሱዙ ፣ መስተንግዶ ፣ ትራንስፖርት ፣ አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ/ከ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ መጻህፍት ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ዕቃዎች፣ ህትመት፣ ሞንታርቦ ፣ ዲኮር ፣ ድንኳን ፣ የጭነት አይሱዙ ፣ መስተንግዶ ፣ ትራንስፖርት ፣ አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

በተጨማሪም በወረዳው ውስጥ የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራች መረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጽህፈት መሳሪያ ፣ የጽዳት ዕቃዎች ሌሎችም በሎት የተዘረዘሩት ናሙና የሚያስፈልጋቸውን በዝርዝር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋና እና ኮፒ በማዘጋጀት በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ወይም በሁለት ወጥ ፖስታዎች /ቴክኒክ/ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በጋዜጣ ቀን 18/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ 10 የስራ ቀናት በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነድ በመውሰድ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 02/12/2017 ዓ/ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ወጣት ማዕከል አዳራሽ በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ብር ሎት 1 /28,000.00/ ሎት 2 /27,500.00/ ሎት 3 /33,400.00 ሎት 4 /12,600.00 ሎት 5 /6250.00 ሎት 6 /16,000.00/ ሎት 7 /5,000,00 በባንክ የክፍያ መያዣ ሰነድ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ለሸነፉት ዕቃ ዋስትና እና ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርበታል፡፡ የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ኦርጂናል ስለመሆኑ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት መወዳደረያ ሰነድ ላይ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማህተም የተደገፈ መሆነ አለበት፡፡
  12. ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ መሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ለመሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞከር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
  13. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልግሎት ብዛት (መጠን) እንዳስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ኦርጅናል የድጋፍ እና አምራች መሆናቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ተጫራቾች የእቃ ዝርዝር ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ መሆኑን እያሳወቅን ከቫት ውጪ ያቀረበ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡
  16. ከሰራተኛ ካፌ የምትወዳደሩ ማቅረብ የሚገባችሁ ለካፌ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በሙሉ ማቅረብ እና በስራ ላይ የሰሩ መሆናቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸኋል፡፡ በመ/ቤቱ መብራት ፣ ውሃ ቤት ኪራይ ነፃ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
  17. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናቶች ይሆናሉ፡፡
  18. መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ - ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ከሎት 8 እስከ ሎት 15 ቲ.ኦ.ቲ/ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ሬሳ በር 2OO ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር 011-126-10-63/011-112-10-50

 

በየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት

 

Save Tender