በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለአበሽጌ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ስር የሚገኙ ት/ቤቶች የአቅም ችግር (ውስንነት) ያለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ የሚሆን ደብተር እስክርቢቶ እና የተማሪ ቦርሳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለአበሽጌ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ስር የሚገኙ ት/ቤቶች የአቅም ችግር (ውስንነት) ያለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ የሚሆን ደብተር እስክርቢቶ እና የተማሪ ቦርሳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጀምሮ ከአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መወሰድ ትችላላችሁ፡፡
ተጫራቾች ፡-
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፈቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 20000 /ከባንክ በተረጋጠ/ሲፒኦ/ በማያያዝ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕና አስፈላጊውን ማስረጃ ጋር በማያያዝ ኦርጅናል ዶክመንት ለዚህ ተብሎ በሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታው የሚከፈተው ማስወታቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ11 ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ወረዳው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0113302079 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ወልቂጤ
