Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline07 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazine አዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security40000.00
  • opening date2025-08-07 00:00:00
  • Categories Safety And Security , Textile, Garment & Leather , Personal Protective Safety Equipment

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት ሠራተኞች የአደጋ መከላከያ እና የደንብ ልብስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የአደጋ መከላከያ እና የደንብ ልብስ ለመግዛት በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ

የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/16B/2017

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት ሠራተኞች የአደጋ መከላከያ እና የደንብ ልብስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርትፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ ፋብሪካ አጠገብ የቀደሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት ኢማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።

ጨረታው የሚዘጋው ነሀሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ 0114709095/ 0114 423608

ፋክስ 0114 421312

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

Save Tender