Tender Detail

Tender Details


በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ዙር ከዚህ በታች የተገለጹትን ጥራት ያለቸውን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ዙር ከዚህ በታች የተገለጹትን ጥራት ያለቸውን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

እነሱም፡-

  • የጽህፈት መሳሪያ (ስቴሽነሪ)፤
  • የደንብ ልብስ
  • የጽዳት ዕቃዎች
  • ቋሚ ዕቃዎች
  • መስተንግዶ
  • ህትመት
  • የትራንስፖርት አገልግሎት
  • የመኪና ቅባቶች
  • የኮምፒዩተር ጥገና
  • የዲኮር ስራ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎችስ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

ለወጣው ጨረታ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፣ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን መስክ የሚገልጽ ያለው ፋይናንሻል ኦሪጅናል በአንድ ፖስታ ፋይናንሻል ኮፒ በሌላ ፖስታ፣ ቴክኒካልና ሲፒኦ በአንድ ፖስታ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ከማለቁ በፊት በፋይናንስ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

  • የጨረታ ሳጥን የሚገኘው በፋይናንስ ጽ/ቤት በግዥ ክፍል ነው።
  • የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለወጣው ጨረታ በሰጡት ዋጋ
  1. ለጽህፈት መሳሪያ (ስቴሽነሪ) 10,000 ብር፣
  2. የደንብ ልብስ 5000 ብር
  3. የጽዳት ዕቃዎች 10,000 ብር
  4. ቋሚ ዕቃዎች 10,000 ብር
  5. መስተንግዶ 10,000 ብር
  6. ህትመት 5000 ብር
  7. የትራንስፖርት አገልግሎት ነፃ
  8. የመኪና ዕቃዎች 5000 ብር
  9. የኮምፒዩተር ጥገና 5000 ብር
  10. የዲኮር ስራ 2,000 ብር በየሎቱ ማቅረብ አለባቸው።
  • አሸናፊው ተጫራች የውሉን 10% ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • በጥቃቅን የተደራጁ በአምራችነት የተሰማሩ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተወዳዳሪዎች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማማለል አይችሉም።
  • መስሪያ ቤቱ ከውሉ በፊት 20% ሊጨምርና ሊቀንስ ይችላል። በተጨማሪም ውል ከተዋዋሉበት ጀምሮ ከአሸናፊው ተጫራቾቾ 25% እስከ (6) ወር ሊጨምር ይችላል።
  • አቅራቢዎች በእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቀደም ብለው ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  • አስተዳደሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻችን፡- መሿለኪያ ሪቼ ጫፍ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ነው።
  • ስልክ፡- +251114621114/ +251922462215

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 10 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender