ወሎ ልማት ማህበር (ወልማ) አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳቡን በታወቀ የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
ወሎ ልማት ማህበር
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ወሎ ልማት ማህበር (ወልማ) አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳቡን በታወቀ የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የ2016 ወይም 2017 ዓ.ም. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- በሂሳብ ምርመራ በቂ ባለሙያና የሥራ ልምድ
- የታክስ መለያ ቁጥር (ቲን)
- ከላይ የተመለከተውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ቢሮ በአካል ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች ለአገልግሎት የሚጠየቅ የገንዘብ መጠን፤ የሚከናወን የኦዲት ሥራ ዝርዝር እና ሥራውን ሠርቶ ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የሚፈጀውን ጊዜ ከጨረታው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከታች በተመለከተው አድራሻ የተጠየቁትን መስፈርቶች በማሟላት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በሥራ ሰዓት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታውም በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ኡካዝ ህንጻ ላይ አምስተኛ ወለል / Mobile +251912044403/
ወሎ ልማት ማህበር
