Tender Detail

Tender Details

  • Company Get As International Plc /ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር/
  • Address ቃሊቲ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911240050
  • Websitehttps://getasplc.com/
  • Deadline02 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-04 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር 19 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Get As International Plc /ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር/


 

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር 19 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ የመነሻ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

የጨረታ ሰነዱን በጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቃሊቲ ትራንስፖርት ዩኒት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት 01 ኦርጅናልና 01 ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት (አስር) 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ከ10ኛው ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 9:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተሽከርካሪዎቹን መመልከት የሚፈልግ ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ዕለት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች በ 10 ቀናት ጊዜ ውስጥ የተሽከርካሪውን ክፍያ አጠናቆ የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ሲቀር ጨረታው ውድቅ ሆኖ ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ በ 07 ቀናት ውስጥ ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡

ድርጅቱ:- የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ: ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቃሊቲ ትራንስፖርት ዩኒት

ስ.ቁ 0911240050 / 0912505149 ወይም 0911205294

 

ጌት አስ ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

Save Tender