Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100000.00
  • opening date2025-08-05 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠመውን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


 

ለሁለተኛ ጊዜ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2017

 

የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠመውን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ፡-

  1. የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ፤ የግብር ከፋይነት ያሟላችሁና የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረት ማቅረብ የምትችሉ፤
  2. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፤
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ በገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማሰራት አለባችሁ፤
  5. የጨረታው አሸናፊ በማስታውቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል፤
  6. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ማየት ይችላሉ፤
  7. ተጫራቾች ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦሪጂናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ በአሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፤
  8. ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  9. ጨረታው የሚፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይተላለፋል፤
  10. ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ቢድ ቦንድ ከሆነ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፤
  • ተሽከርካሪው የህይወት ታሪክ አለው ስለዚህ በቀጥታ የስም ዝውውር የሚደረግ ይሆናል፤
  • ማስታወቂያ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሚጋብዝ ቢሆንም ሌሎች ማንኛውም ፈቃድ የሌለው ግለሰብ መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፤

ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 0113360146/0113360631

 

በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender