በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎችንና ዕቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎችንና ዕቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ ሎት 2 የሕንፃ መሣሪያዎች ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሎት 4 የተለያዩ የህትመት ዓይነቶች ሎት 5 የግንባታ ጥሬ ዕቃዎች ሎት 6 የሻይ ቡና መስተንግዶ ሎት 7 ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን ነጭ ሸራ ድንኳን ከነስቴጅ እና ፕላስቲክ ወንበሮችን ለመከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ከዚህ በፊት ላከናወኗቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 /አራት ሰዓት/ ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የ20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ርክክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0461800863 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
