Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት
  • Address በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠ/አ ቢሮ ቁጥር 304፡ ትግራይ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251342406712
  • Website
  • Deadline05 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security20.00
  • opening date2025-08-05 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቐለ ሪጅን ንብረት የሆኑት የተለያዩ ቀላልና ከባድ ያገለገሉ 7 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር መቐ/ሪ/ን/ማ/02/2018 - ሎት-2

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቐለ ሪጅን ንብረት የሆኑት የተለያዩ ቀላልና ከባድ ያገለገሉ 7 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርቦ መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ የዛምራ ኮንስትራክሽን ሕንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ቀርበው የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ዝርዝር የተሽከርካሪዎች መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን በመቐለ ከተማ 05 ቀበሌ ደንበስኮ ፊት ለፊት የሚገኝ የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዕቃ ግምጃ ቤት ቅጥር ግቢ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት (MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY) ስም ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ በመቐለ ከተማ ከፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኝ ዛምራ ኮንስትራክሽን ህንፃ 3ኛ ፎቅ የመቐለ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304 በመምጣት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0342406712 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት

 

Save Tender