Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
  • Address ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115512938
  • Websitehttps://epse.gov.et/
  • Deadline15 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-15 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Safety Clothe And Shoes

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ ትጥቆች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ ትጥቆች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ምድብ 1 የተለያየ የሥራ አልባሳት

ምድብ 2. የድርጅቱ ዓርማ የሚታተምበት መለዮና ከረባት

ምድብ 3. የተለያዩ ጫማዎች (የሥራና የሴፍቲ ጫማዎች)

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN No) ያላቸው
  2. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለምድብ 1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ፣ ለምድብ 2 ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣ እና ለምድብ 3 ብር 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 09/12/2017 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በዚሁ ቀን 09/12/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ለሶስቱም ምድብ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር 0115525405/011-551-32-88

ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

 

Save Tender