የክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤተ-ክርስቲያን የህፃናት እርዳታ ድርጅት በልጆች ዙሪያ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ማህበሩ እ.ኤ.አ. የ2025/26 ጀምሮ ላሉት ተከታታይ ሶስት አመታት ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል።
የክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤተክርስቲያን የሕፃናት እርዳታ ድርጅት
የውጭ የሒሳብ ኦዲተር
የጨረታ ማስታወቂያ
የክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤተ-ክርስቲያን የህፃናት እርዳታ ድርጅት በልጆች ዙሪያ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ማህበሩ እ.ኤ.አ. የ2025/26 ጀምሮ ላሉት ተከታታይ ሶስት አመታት ሒሳቡን በውጭ ኦዲተር ማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው
- የሙያ ብቃትና በሕጋዊነት ታውቀው በመንግስት መመዝገቡን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርብ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የታደሰ ፍቃድ ያለው
- የኦዲት በቂ የሥራ ልምድ ያለው /ባለሙያ ያላቸው
- ከዚህ በፊት በድርጅት ሒሳብ ሰርቶ የሚያውቅ
ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልጽ በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለከቱ እናሳውቃለን፡፡
* የልማቱ ዋና ጽ/ቤት ጎፋ መብራት ሀይል አዋሽ ባንክ ፊት ለፊት ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤተ-ክርስቲያ ዋና ጽ/ቤት በአካል ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ:- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913178378/0913221141/
0114661180 መደወል ይቻላል
