በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪያ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ መዋቢያና የንጽሕና መጠበቂያ፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና ምግብ ነክ ዕቃዎች በግልጽና ሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 03/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ የመገናኛ መሣሪያ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ መዋቢያና የንጽሕና መጠበቂያ፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና ምግብ ነክ ዕቃዎች በግልጽና ሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሀዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ግልጽ ጨረታ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም የሐራጅ ጨረታ ተጫራቾች ለኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 50,000 (ሃምሣ ሺህ ብር) አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ኮድ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (C.PO) ማሠራት የሚጠበቅበት ሲሆን የአንድ ኮድ ብቻ አሠርቶ በመምጣት አንዱ ሳይሳካ ወደ ሌላው ኮድ አዛውሮ መጫረት አይችልም፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው (ሰባተኛው ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የሥራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8ኛው /ስምንተኛው/ ቀን ግልጽ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 በሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የሐራጅ ጨረታው የግልጽ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይካሄዳል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-0462125396
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
