Tender Detail

Tender Details

  • Company የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-67-81-75
  • Website
  • Deadline28 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security50000.00
  • opening date2025-07-28 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር የስፖርት ትጥቅ ልብስ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

5ኛ ዙር 2017 ዓ.ም

 

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር የስፖርት ትጥቅ ልብስ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፤

ሎት 1 የስፖርት ትጥቅ ልብስ ግዥ (CPO-50,000)

ስለዚህ በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሀጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል።

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁባቸውን ዕቃዎች መጫረቻ ሠነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
  6. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከላይ በተገለፀው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ለአንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ውስጥ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆኑን አለመሆኑን ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  11. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ ቁጥር፡- 011-8-67-81-75

 

የየካ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን

 

Save Tender