Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህበር
  • Address ከኡራኤል ቤተከርስቲያን ወደ ካዛንቺስ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ባህራን ሞል 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 እና 507 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0902-455555
  • Website
  • Deadline22 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-22 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ የሂሳብ አዋቂዎች እና አዲተሮች ማህበር የ 2017 ዓ.ም በጀት አመት ሂሳብ ለማስመርመር (አዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህበር


 

የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የሂሳብ አዋቂዎች እና አዲተሮች ማህበር የ 2017 ዓ.ም በጀት አመት ሂሳብ ለማስመርመር (አዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል።  ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ስራ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የታክስ መለያ ቁጥር (Tin No) ያላቸው
  2. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የታደሰ ሙያ ፈቃድ ያላቸው ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የተሟላ የቴክኒክ እና የፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሰጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  4. ጨረታው በ5ኛው ቀን ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ እለት ከቀኑ 10፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታው ውጤት የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንደተጠናቀቀ የሚገለፅ ሲሆን በቴክኒክ ግምገማው ያላለፈ ተወዳዳሪ ለፋይናንሻል ውድድር አይቀርብም፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልፅ ፕሮፖዛል በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለከቱ እናሳስባለን ፡፡

አድራሻ፡- ከኡራኤል ቤተከርስቲያን ወደ ካዛንቺስ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ባህራን ሞል 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 እና 507 ወይም በስልክ ቁጥር 0902-455555 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎችና ኦዲተሮች ማህበር

 

Save Tender