በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት 2013 ዓ/ም 2014 ዓ/ም፥ 2015 ዓ/ም፣ 2016 ዓ.ም እና 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
የቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የውጭ ኦዲት ስራ አገልግሎት ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት 2013 ዓ/ም 2014 ዓ/ም፥ 2015 ዓ/ም፣ 2016 ዓ.ም እና 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡
- ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የአዲት የሙያ ብቃት ፈቃድ ያለው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን አስገዳጅ የሆነ እና አሰራር የዳበሩ ህጋዊ መስፈርት የሚያሟላ
- አዲቱ የሚደረገው በቦዲቲ ከተማ በሚገኘው ድርጅት ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀን በአየር ላይ ከዋለ ቀን ጀምሮ ማስታወቂያውን አይተው በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር ከቢሮ ቁጥር 03 በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጨረታው ከሚያቀርቡት የአገልግሎት ዋጋ ላይም 2% /ሁለት በመቶ/ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሠረት በመሙላት በስራ ቀናትን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 03 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በመጨረሻው ቀን ብቻ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ነው።
ማስገንዘቢያ፡-
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር +251921832296 እና +251919216616 በመጠቀም ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቦዲቲ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ቦዲቲ ከተማ
