በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የሳኒቴሽንና ሃይጅን ዕቃዎች በተለያዩ ሁለት ወረዳዎች አለታ ጩኮ፣ ሸበዲኖ ለኩ ወረዳ የሚሰራጭ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የሳኒቴሽንና ሃይጅን ዕቃዎች በተለያዩ ሁለት ወረዳዎች አለታ ጩኮ፣ ሸበዲኖ ለኩ ወረዳ የሚሰራጭ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፣
- ሲሚንቶ በኩንታል
- አሸዋ በሜትር ኩዩብ
- ፌሮ ብረት ባለ8 ሚሊ ሜትር
- የንግድ ፍቃዳቸው የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ/ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ጨረታውን በክልል ሲዳማ ጤና ቢሮ በማቅረብ ለግዥ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 27 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ CPO 2% የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንቸው አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻው ኤንቨሎኘ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፣ በመሆኑም ከዚህ በላይ ከተገለጸው ውጪ የሚያቀረቡ ከውድድር ወጪያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱ በሚያቀርቡት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱ ስምና ማህተም በግልፅ መቀመጥ አለበት፣
- ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ ከ4-6፡00 ሰዓት ድረስ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን በማስገባት በተጠቀሰው ሰዓት ይታሸጋል፤ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀናት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462126783 ይጠይቁን
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
