የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመግዛት ካቀደው ግዥ ውስጥ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃ ከህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለመግዛት ካቀደው ግዥ ውስጥ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃ ከህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት :-
- ተጫራቾች ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከመንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ከሲዳማ ባንክ ብቻ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ CPO ወይም ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኙን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በአንድነት ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ
አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ይርጋዓለም
