Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት:-

ሎት 1:- የመኪና ጎማና ባትሪ                         ሎት 5፡- የጉልበት ስራዎች

ሎት 2፡- የህትመት ስራዎች                          ሎት 6፡- የከባድ መኪና ጥገና

ሎት 3፡- የዲኮር እና መድረክ ዝግጅት                ሎት 7፡- የከባድ መኪና ጎማ ጥገና (ጎሚስታ)

ሎት 4፡- የመኪና ኪራይ                              ሎት 8፡- የከባድ መኪና እጥበት

በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል።

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  3. ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ጨረታው በአንድ ኢንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናል ዶክመንት እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት1 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፡ ከሎት2፣3፣4፣5፣7 እና ሎት 8 የሆኑትን ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ እና ሎት 6 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በስራ ኤንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ነገርግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች ሎት 1 የመኪና ጎማና ባትሪ እና በሎት 2 የህትመት ስራዎች ላይ የሚጫረቱ የዕቃ ናሙና /sample/ የጨረታ ጊዜው ሳያልቅ የማቅረብ ግዴታ አላቸው።
  11. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ።
  12. መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
  13. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ፤ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።

አድራሻችን፡-

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 504

በስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

ለበለጠ መረጃ፡-011-835-88-99 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender