አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የፅህፈት መሣሪያዎች፤ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሀም የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AIC ፡- 0007/2025
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሀ. ሎት-1 የፅህፈት መሣሪያዎች
ለ. ሎት-2 የፅዳትና ሪፍሬሽመንት እቃዎች
ሐ. ሎት-3 የህትመት ውጤቶች
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኩባንያው ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም።
- ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ ሙሉ ለሙሉ ለተጫራቾች ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት ስለመሆናቸው ካረጋገጠ በኋላ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ገዝተው የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት እና ብዛት የሚገልፅ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በስራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ሀምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል።
- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያ ፣ የሪፍሬሽመንት እና የፅዳት እቃዎችን ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ እንዲሁም ለህትመት ውጤቶች ከ15 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች እና የሪፍሬሽመንትና የፅዳት እቃዎችን ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ናሙና እንዲሁም የህትመት ውጤቶቹ በኩባንያው ናሙና መሰረት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ኩባንያዉ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116 611877/0116 637485/
0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ
