Tender Detail

Tender Details


የአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያገለገሉ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ዩፒኤስ፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Amanuel Mental Specialized Hospital (የአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)


 

ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያገለገሉ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ዩፒኤስ፣ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  • የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ አማኑኤል አእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በ2 ኮፒ በማቅረብ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት መሙላት አለባቸው በሁለት ኮፒ ሞልቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  • ብረታ ብረት እና የመኪና መለዋወጫ በተመለከተ ለብረታ ብረት አቅላጭ ድርጅቶች /ኢንዱስትሪዎች/ በውድድሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን አውቆ መወዳደር አለበት፡፡
  • ጨረታው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአማኑኤስ የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender