Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም ሎት 1፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 2. የህትመት አገልግሎት ሎት 3. ለቢሮ የመስተንግዶ አገልግሎት እና ሎት 4፡ የሰራተኛ ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/774 2018 ዓ.ም

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም ሎት 1. የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 2. የህትመት አገልግሎት ሎት 3. ለቢሮ የመስተንግዶ አገልግሎት እና ሎት 4፡ የሰራተኛ ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት (VAT) ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ፤
  5. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ከ (egp/www.ppa.gov.et) ፕሪንት አድርገው ማቅረብ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና እንዲሁም ናሙና ለሚጠይቁ፤
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት አገልግሎት ለሎት 1. የትራንስፖርት ብር ብር 5,000 ለሎት 2. የህትመት አገልግሎት ብር 5,000. ብር ለሎት 3. ለ ቢሮ መስተንግዶ ብር 5,000 ብር እንዲሁም ለሎት 4. ለሎት አራት የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተረጋገጠ በባንክ ትእዛዝ CPO ብቻ ማዘዥያ የክፍያ (አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር) በሚል አሰርተው ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያነት 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 / አስር / ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 017 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ ለሚሆኑባቸው አገልግሎቶች ለስድስት ወር ውል ወስደው አገልግሎቱን የሚያቀርቡ ሲሆን የመጫረቻ ዋጋቸውም ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  10. የሰራተኞች ካፍቴሪያ ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ካፍቴሪያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግብአቶችን ማለትም ከወንበርና ጠረጴዛ ውጭ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡
  11. ከጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ / ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ቃሊቲ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገባ ብሎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 011-471-79-31

 

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender