Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011155344949
  • Website
  • Deadline23 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-23 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ለልምምድና ለውድድር የሚሆን የስፖርት አልባሳት ወይም ትጥቅ ከሀገር ውስጥ የስፖርት ትጥቅ አምራች ከሆኑ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኤስክ/ግጨ-01/2017

 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ለልምምድና ለውድድር የሚሆን የስፖርት አልባሳት ወይም ትጥቅ ከሀገር ውስጥ የስፖርት ትጥቅ አምራች ከሆኑ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እና የጨረታ መዝጊያ ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ፡፡

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የሚገኝበት ቦታ

መለኪያ

ብዛት

1

Complete sportswear Uniform (ሙሉ ቱታ)

ለገሀር

በቁጥር

370

2

Dining – hall jersry (የምግብ ቤት ቲ-ሸርት ባለ ኮሌታ እና አንገቱ ኦ ሁለት ዓይነት)

ለገሀር

በቁጥር

640

3

የውድድር ማሊያ ከነቁምጣው (Jersey and shots) በሶስት ዓይነት ለእግር ኳስ ቡድን

ለገሀር

በቁጥር

135

4

የውድድር ማሊያ ከነቁምጣው (Jersey and shots) ሁለት ዓይነት ለእግር ኳስ እና ጠረጴዛ ኳስ እና ጠረጴዛ ኳስ ቡድን

ለገሀር

በቁጥር

280

5

የሟሟቂያ ማሊያ ሁለት (2) አይነት ለእግር ኳስ ቡድን

ለገሀር

በቁጥር

40

6

Trialing Jersey and shots (የልምምድ ማሊያ ከነቁምጣው) ሁለት ዓይነት ለእግር ኳስ፤ ለጠረጴዛ ኳስ እና አትሌቲክስ ቡድን

ለገሀር

በቁጥር

600

7

ጃፖኒ ማሊያ ለአትሌቲክስ ቡድን

ለገሀር

በቁጥር

160

8

Basic Soccer Sock (ኳሶተኒ) ለእግር ኳስ ቡድን

ለገሀር

በጥንድ

290

9

(የአሰልጣኝ ማሊያ ከነቁምጣው) ሁለት ዓይነት

ለገሀር

በቁጥር

90

 

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (Ethio electric sport club No, 1000252229713) የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ለገሀር ባቡር ጣቢያ አጠገብ በሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት በመምጣት የስፖርት ትጥቆችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመደበኛ የስራ ሰዓት የስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለገሀር በሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው::
  5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ለገሀር ባቡር ጣቢያ አጠገብ በሚገኘው ስፖርት ክለቡ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
  6. ስፖርት ክለብ ለሚፈጽመው ለስፖርተኞች አገልግሎት የሚሆን የልምምድ እና የመወዳደሪያ ትጥቅ ግዥ ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንስ ሰነዳቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪ ለሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ናሙና ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሆንኑ አስመልክቶ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የሀገር ውስጥ የስፖርት ትጥቅ አምራችነት የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-1-55-34-49-49 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ

 

Save Tender