Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ በሻሌ ወረደ 04 ውሃ ታንከር አካባቢ ህንጻ ቁጥር 13 አንደኛ ወለል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913489663
  • Website
  • Deadline19 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security25000.00
  • opening date2025-07-19 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Wood And Wood Working

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ትርንጫፍ ጽ/ቤት ቡልቡላ ሳይት የሚገኘውን መጋዘን ተጫራቹ አራሱ አፍርሶ ቆርቆሮውን ፣ የቋሚ እና የማገር እንጨቶቹን ለሚገዛ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ምስራቅ/ቅ/ፅ/ቤት 004/2017

 

በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ትርንጫፍ ጽ/ቤት ቡልቡላ ሳይት የሚገኘውን መጋዘን ተጫራቹ አራሱ አፍርሶ ቆርቆሮውን ፣ የቋሚ እና የማገር እንጨቶቹን ለሚገዛ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቹ መጋዘኑ የሚገኝበት ቦታ በመገኘት ምልከታ በማድረግ የእቃ /የቆርቆሮ/ ሽያጭ መጫረት ይችላል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ
  5. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታውን ዝርዝር የጨረታው ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ አስከ አርብ ከ2፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ በሻሌ ሳይት ውሃ ታንከር አካባቢ በፕሮጀክቱ ጽ/ቤቱ ህንጻ ቁጥር 13 ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፡፡
  7. ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሽያል ሠነዶች ተለይቶ በተለያየ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናሻል ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  8. ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ ከ2፡00-11፡00 ድረስ የጽ/ቤቱ ቢሮ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ (ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት /መሆኑን እንገልፃለን።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል። እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የአሸነፉባቸውን አገልግሎት የውል ማስከበሪያ ለማስያዝና ከመስሪያ ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት ለመፈፀም መስማማት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ በሻሌ ወረደ 04 ውሃ ታንከር አካባቢ ህንጻ ቁጥር 13 አንደኛ ወለል በሚገኘው ጽ/ቤታች

ለበለጠ ማብራሪያ:- 0913-48-96-63/0911-06-33-70/ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE