Tender Detail

Tender Details

  • Company SOUTHWEST CONSTRUCTION CORPORATION (የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦንጋ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0927549359
  • Websitehttps://southwestcorporation.com/
  • Deadline16 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-17 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ ሰነድ በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ወይም አዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

SOUTHWEST CONSTRUCTION CORPORATION (የደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)


 

ለሂሳብ ምርመራ /ኦዲት/ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመ/ቤቱ ሥም: ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ደምኮኮ)

የጨረታ አይነት: ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር: 006/2017

ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ ሰነድ በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ወይም አዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት:-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፊኬት ያላቸው፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  • የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው፣
  • ከተለያዩ ተቋማት የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት/ በማድረግ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ፣
  1. የጨረታ ሰነድ የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ -
  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት/ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000615509209 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ አካባቢ ከሚገኘው ደቡብ ምዕራበ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ -
  1. ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፡-
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከቀኑ ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው በማግስቱ በ17ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • 17ኛው ቀን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • በጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚገኙ ህጋዊ ወኪሎች የውክልና ማረጋገጫ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
  • ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
  1. የጨረታ ዋስትና
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ሁለት ከመቶ /2%/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ከ90 /ዘጠና/ ቀናት ወይም ሦስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በባንኩ ዋና መ/ቤት የተረጋገጠ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
  1. የጨረታ ሠነድ አቀራረብ ሁኔታ፡-
  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት# የግብር ከፋይነት ሠርተፊኬት እና የታከስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO ከዋና /ኦርጂናል/ የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው። ፋይናንሻል ዶክሜንት ዋና እና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
  • ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡
  • የኮፒና ኦርጅናል መለያየት ካለ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ካላስያዙ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
  • ባቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያ አና የመጫረቻ ሰነድ ላይ እራስዎ ስለመሙላትዎ የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም ፊርማ እና ማህተም ማረጋገጥ ይኖርበታል።
  • በጨረታ ሰነድ ላይ ቅሬታ ካለ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል
  • ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን /ቦንጋ/

 

Save Tender