Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-122-00-20
  • Websitehttps://www.oromiaforest.et/
  • Deadline11 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-11 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት መጋዳ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)


 

የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

OFWE/GU-01/2018 ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት መጋዳ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና TIN number ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይል።
  3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፣ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111 24 02 49 በመደወል ማጠየቅ ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

 

Save Tender