የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፤ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ምግብ ነክ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 48/2017
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፤ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ምግብ ነክ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር) 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO ፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው መጠን ዋስትና (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው (ሰባተኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8ኛው (በስምንተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4:05 በሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ጊቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-5396 / 046-212-6595
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
