Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
  • Address 6ኪሎ አካባቢ ከፈረንሳይ ታክሲ መያዥ አለፍ ብሎ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111261615
  • Websitehttps://aaceb.gov.et/
  • Deadline14 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-15 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Maintenance And Repair , Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሎት 1 የሰራተኞች የመዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 2 የጀነሬተር የጥገና አገልግሎት ግዥ ሎት 3 ለእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ፣ ለገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት እና ለገላን የብርሃን ዓይነ-ስውራን ትምህርት ቤት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ ማግኘት ይፈልጋል።

Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሎት 1 የሰራተኞች የመዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 2 የጀነሬተር የጥገና አገልግሎት ግዥ ሎት 3 ለእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ፣ ለገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት እና ለገላን የብርሃን ዓይነ-ስውራን ትምህርት ቤት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ግዥ ማግኘት ይፈልጋል። ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ዕቃ ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን
  2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ /CPO/ ለሎት 1 ፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 ለእያንዳንዳቸው 50,000.00 ብር ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከቢሮአችን ከመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት እና ቢሮ ቁጥር 101 ሰነዱን በሶፍት ኮፒ፣ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፣
  4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ለሎት 1፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 ቴክኒካልና ፋይናሽል ኦርጂናልና ኮፒ ሰነድ ፖስታ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
  5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ16ኛው ቀን/ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል። ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣
  6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣
  7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ በ7 /ሰባት/ ቀናት
  8. በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  9. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ዝግጁ መሆን አለበት፤
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

በስልክ ቁጥር 011 122 6456

አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender