በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጸዳት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ የመካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል የጽዳት ስራን አውት ሶርስ በማድረግ ለአንድ አመት ቆይታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጸዳት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መወዳደር ይችላል።
- በመ/ሰ/ጠ/ሆስፒታል ቅጥር ግቢ የሚገኘውን እና የነማጣ ካምፕ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችና የቅጥር ግቢውን ንፅህና የሚጠብቅና የሚያፀዳ።
- በጥቃቅን አነስተኛ ህግ በሚያዘው መሰረት የተደራጀና መረጃ ማቅረብ የሚችል በመመሪያው መሰረት ይፈጸማል።
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ሆስፒታሉ በሚፈልገው መሰረት የተመረጠውን ከለርና ስፌት የደንብ ልብስ በስራ ሰዓት በራሱ ወጭ አሟልቶ መልበስ የሚችል።
- ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው።
- ማንኛውንም የጽዳት ዕቃዎች ለምሳሌ፡- በረኪና፣ ኦሞ፣ ላርጎ፣ ሺም፣ ዲቶል፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ፣ መወልወያ እና ባልዲና ፎጣ በራሱ ወጭ አሟልቶ ማጽዳት የሚችል።
- በጽዳት ስራ ላይ የሠራተኞች ብዛት 12 የሚሆንና ቅዳሜ፣ እሁድ፣ የህዝብ በዓላት እና የአዘቦት ቀን በ24 ሰዓት ውስጥ በጽዳት ስራ ላይ መገኘት አለባቸው።
- የመጸዳጃ ቤቶች ንጽህና በመጠበቅ የሽንት ቤት መርዝ በመጠቀም መፀዳጃ ቤቶች ሽታ አልባ መደረግ አለባቸው።
- የበረኪና አንድ ለዘጠኝ ውህደትን በመጠቀም የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን በመወልወል ንፅህናቸውን የሚጠብቅ።
- አሸናፊው ተጫራች (ማህበሩ) በጽዳት ወቅት በየአገልግሎት መስጫ ከፍሎች የሚገኙትን ንብረቶች የጽዳት ሠራተኛው በእንዝላልነትና በግዴለሽነት ምክንያት ለጠፉ ለሚጠፉ ሠነዶች፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች የመንግስት ሀብትና ንብረት የሚከፍልና በህግ የመጠየቅ ግዴታ አለበት።
- በሆስፒታሉ ህግና ደንብ መሰረት ተገዥ የሆነና ሌሎች ከጽዳት ጋር የተያያዙ ስራዎችንና የሚሰጠውን ማንኛውንም ተግባር ተቀብሎ መፈፀም የሚችል።
- ማህበሩ መድቦ በሚያሰራው የጽዳት ሠራተኞች ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ማህበሩ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
- በወር ለአገልግሎትና ለጽዳት ዕቃዎች ግዥ መጠየቂያ ደመወዝን ጨምሮ ሊከፍለው የሚችለውን ገንዘብ መጠን በኢትዮጵያ ብር ጥቅል ድምር በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሰነድ በወር እና በዓመት የሚለው ጨረታ ሰነድ ላይ በትክከል መሙላት አለበት።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከመሥሠ/ጠ ሆ/ ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሠነድ ላይ በመሙላት በደንብ በታሸገ ፖስታ መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰዓት ከግፋን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፤ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል ቅዳሜ እና እሁድ (በዓል) ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ የግፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 34 37 02 54/ 09 14 34 43 06/033 220 0834 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
መካነ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል
