Tender Detail

Tender Details

  • Company Abay Construction (አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ህዳሴ ሰፈር ታክስ ማዞሪያ 190 ሜትር አልፍ ብሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0918216183
  • Websitehttps://abayconstruction.org.et/
  • Deadline08 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-08 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

አባይ ኮንስትራክሸን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡

Abay Construction (አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)


 

የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ

ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

አባይ ኮንስትራክሸን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

  1. የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር (TIN) እና የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና መያዊ ስነ-ምግባራቸውን በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
  5. ተጫራቾች ለሚሞሉበት ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሸን ኃ/የተ የግ ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ፣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመዉሰድ መጫረት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒከ ማወዳደሪያ ሰነድ “፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond) ማሲያዣን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 19 ግዥ የስራ ሂደት ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ዉጭ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 19 ግዥ የስራ ሂደት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 0991021430 ወይም በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
  2. ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የግል ማህበር ባህር ዳር ከተማ

 

አባይ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

 

Save Tender