የአሳላ መምህራን ት/ኮሌጅ ያገለገሉ ወይንም አገልግሎት የጨረሱ ኮምፕተሮችን እና ሌሎች በመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Asella College of Teachers Education (አሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአሳላ መምህራን ት/ኮሌጅ ያገለገሉ ወይንም አገልግሎት የጨረሱ ኮምፕተሮችን እና ሌሎች በመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት መወዳደር ትችላላችሁ።
- ለተገለጹት እቃዎች በደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ፤ በማሸን ጥገና እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረት እና ተዛማች ንግድ ሥራ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በኮሌጁ ስም ባንክ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኮሌጁ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ማቅረብ እና ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ15ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኮሌጁ አዳራሽ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ታዋቂ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(CPO) በኮሌጁ ስም ገቢ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች በአንድ ወር ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ማንሳት ይኖርበታል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 30 107 417 ይጠይቁ።
አሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ
