በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገባ/ዲዲሳ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ ግንዲላ እንዲሁም ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ሲግሞ ሰጠማ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ እና የ “Grevillea robusta” ድብልቅ ግንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂ
የጨረታ ቁጥር OFWE/GU-14/2017
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገባ/ዲዲሳ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ ግንዲላ እንዲሁም ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ሲግሞ ሰጠማ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ እና የ “Grevillea robusta” ድብልቅ ግንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ እና ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 124 0249 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
