የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለነዳጅ ዴፖ እና ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ክፍት ቦታ በክልል ኤርፖርቶች (ላሊበላ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሀር፣ ጂንካ፣ ነቀምት፣ ሮቤ ጎባ፣ ሽሬ፣ ደሴ እና ሁመራ ኤርፖርቶች) በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
ለአውሮፕላን ነዳጅ ዲፖ አገልገሎት ቦታ ኪራይ ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T543
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለነዳጅ ዴፖ እና ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ክፍት ቦታ በክልል ኤርፖርቶች (ላሊበላ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጎዴ፣ ቀብሪደሀር፣ ጂንካ፣ ነቀምት፣ ሮቤ ጎባ፣ ሽሬ፣ ደሴ እና ሁመራ ኤርፖርቶች) በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- በነዳጅና እና ነዳጅ አቅራቢነት ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- ሶስት (3) ዓመት የአገልግሎት የስራ ልምድ በነዳጅ እና ነዳጅ አቅራቢነት ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T543 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ከታች ባለው ኢሜል አድራሻ ፍላጎት በማሳወቅ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-89-18 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኢሜል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
