Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline01 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-01 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


 

የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አደኢ ግ/ጨ-019/2017

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።

  1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax identification Number (ቲን ነምበር) ያለው፣
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
  5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት (የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ) (የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ) እና (የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond) ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሽገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 13 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ በ10 ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የእርፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል።
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 058 226 49 62 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender