በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት የሚቆይ የሰራተኞች ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ ለአንድ አመት የሚቆይ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር፡- 07/2017
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት የሚቆይ የሰራተኞች ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ ለአንድ አመት የሚቆይ የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶች ያቀርባሉ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን ሰርተፍኬት ያላቸውና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለሎት 1 የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ፣ የኦፕሬተርነት ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም የንግድ ስራ ፈቃዳቸው የየብስና ተዛማጅ አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው ለንግድ የሚል ወይም የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ሃገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሆኖ ሊብሬው የመኪና ማከራየት የሚል አመታዊ የምርመራ ተለጣፊ ምልክት ቦሎ/ያደረገ፣
- ለሎት 2- የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለአንድ ዓመት የሚቆይ የተሸከርካሪ ጥገና አገለግሎት በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ማለትም ደረጃ ሶስት እና ከዚያ በላይ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 2- የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) እና ለሎት 1 ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ መስመር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 / አንድ መቶ ብር / ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በአፄ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ ዘመን ኮንስትራክሽ ድርጅት ጎን በሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላት በሚገባ በኤንቨሎፕ/ ፖስታ በማሽግ እና ተቋሙ ያዘጋጀው ሰነድ ዋጋ መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ 3ኛ ፎቅ የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 306 ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል፣ ነገር ግን 16 ኛው ቀን የህዝብ በዓል/እሁድ ከሆነ በ17ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ ማስረጃዎች ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 320 7051/058 320 6641/058 226 3346/
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
