ቅማንት ልማት ማህበር /ቅልማ/ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የገቢና የወጪ የሂሳብ እንቅስቃሴ በተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ የገቢና ወጪ ሂሳቡን ማስመርመር ይፈልጋል።
የቅማንት ልማት ማኅበር (ቅልማ)
ግልፅ የገቢና የወጪ የሂሳብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ
ቅማንት ልማት ማህበር /ቅልማ/ በኢፌዴሪ የተባ ሃገር በቀል ድርጅት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 68/1 መሰረት በመዝገብ በቁጥር 2951 በኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣል ዳግም ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሲሆን የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የገቢና የወጪ የሂሳብ እንቅስቃሴ በተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ የገቢና ወጪ ሂሳቡን ማስመርመር ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማለትም
- ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ቲን ነበር ያለው
- የዘመኑ የስራ ግብር የከፈለ
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የተመዘገበ
- ከኦዲት በኋላ የተሟላ የሂሳብ ሪፖርት የሚያቀርብ
- ሂሳቡን በ5 ቀን ውስጥ ሰርቶ ማቅረብ የሚችል
- ጨረታውን አሸናፊ የሆነ ጽ/ቤታችን ካመነበት ለቀጣዩ በጀት አመት ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪል ባይገኝ ጽ/ቤታችን ፖስታውን የመክፈትና የማወዳደር መብት አለው
- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በሰም በታሸገ ዋናው ፖስታ ዋናውን እና ኮፒውን ዘወትር በስራ ሰዓት ጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 አውቶፓርክ ጽ/ቤታችን በአካል ማስገባት ይችላሉ
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጫ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0918771758 ወይም 0948845244 ላይ ይደውሉ
የቅማንት ልማት ማኅበር (ቅልማ)
