በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለማዘጋጃ ቤት የተለየዩ እቃዎች ሎት 01 ለካዳስተር ሲስተም ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እቃ እና ሎት 02 የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ጎማ በጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለማዘጋጃ ቤት የተለየዩ እቃዎች ሎት 01 ለካዳስተር ሲስተም ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እቃ እና ሎት 02 የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ጎማ በጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- በመስኩ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፣
- በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፣
- የጨረታ ዋስትና ለካዳስተር ሲስተም ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒከስ እቃ 40,000 እና የእሳት አደጋ መከላከያ መኪና ጎማ 30,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0467710211 ይደውሉ፡፡
በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
