በኢትዮጵያ ደን ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዕከል ለመሥሪያ ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (ሴፍቲ ጫማ ፣ ጃኬት ፣ ጉዋን ፣ ቱታ ፣ ሸሚዝ እና የመሳሰሉትን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ደን ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ደን ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዕከል ለመሥሪያ ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (ሴፍቲ ጫማ ፣ ጃኬት ፣ ጉዋን ፣ ቱታ ፣ ሸሚዝ እና የመሳሰሉትን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በጨረታ ለመሳተፍ ሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የገንዘብ ሚ/ር ከአቅራቢዎች ዝርዝር የሙያ ዘርፍ ተመዝጋቢ የሆኑና ሁኔታውን የሚያስረዳ የምስክር ወረቅት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብይት መጠኑ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) እና ከዚያ በላይ የሆኑና 20,000 /ሃያ ሺ/ ብር አግባብ ካለው መንግሥታዊ ወይም የግል ባንክ ሲፒዮ /ቢድ ቦንድ/ ማስያስዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ መስሪያ ቤታችን በሚገኝበት ማለትም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ፊት ለፊት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ደን ልማት ቁጥር ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የደንብ ልብስ ዋጋ በሙሉ ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታው የጨረታ ታሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከጧቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፣
- ጨረታው በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የደንብ ልብሱን ሙሉ በሙሉ ለማዕከሉ ማስገባት አለበት፤
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዕቃ ግዥ ባለሙያ ግርማ አድማሱ 0911603080 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ላምበረት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ኢትዮ ቻይና ኮሌጅ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ፊት ለፊት
በኢትዮጵያ ደን ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዕከል
