በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ለደ/3 ሆስፒታል የሚውሉ የታካሚ ቀለቦች ሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ እና ደ/3 ሆስፒታል ሲቪል ሰራተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና መጫረት ይፈልጋል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- A-01/2017
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡
- ለደ/3 ሆስፒታል የሚውሉ የታካሚ ቀለቦች
- ለሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ እና ደ/3 ሆስፒታል ሲቪል ሰራተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የታካሚ ቀለቦችን ለመግዛት እና ለደ/3 ሆስፒታል ሲቪል ሰራተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች መጫረት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ የታካሚ ቀለብ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/ ሁሉም ንግድ ፈቃዶች በተናጠል ኮፒ መደረግ አለባቸው፡፡ እንዲሁም፡-
- ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ግብር ስለመክፈላችሁና ጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ /ማስረጃ/፤
- ወርሃዊ የቫት ሪፖርት የተደረገበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለሰ/ምዕ/ዕዝ ጠ/መምሪያና ደ/3 ሆስፒታል ሲቪል ሰራተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች፡-የምዝገባ ወረቀት፣ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/፤ የተሽከርካሪ መረጃ እና የመድን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
1ኛ. ባለ 60 ወንበር መኪና 60 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቢያንስ በቀን 100 ኪሎ ሜትር አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 04
2ኛ. ባለ 14 ወንበር መኪና 14 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቢያንስ በቀን 100 ኪሎ ሜትር አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 02
3ኛ. ባለ 12 ወንበር መኪና 12 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቢያንስ በቀን 100 ኪሎ ሜትር አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 01
4ኛ. ባለ 27 ወንበር መኪና 27 ሰው የመጫን አቅም ያለው ቢያንስ በቀን 90 ኪሎ ሜትርእና 68 ኪሎ ሜትር አገልግሎት የሚሰጥ ብዛት 02
ከባህር ዳር ከተማ መኮድ ካምፕ ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ስለሚፈለግ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት /GARANTE 1. የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለቦች ብር 500,000.00፤ 2 ሲቪል ሰራተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሰርቪሶች ብር 75,600,00 ጨረታው ከአርብ 13/10/2017 እስከ ረቡዕ 25/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሽጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ሃሙስ 26/10/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ/ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ.ም በሃገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር፡- 058-3-21-65-82/ 058-3-21-28-92
በመከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
