በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገሉ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች፣ ኮምፕረሰሮች፣ ብረታ ብረቶች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያገለገሉ የተለያዩ የስፌት ማሽኖች፣ ኮምፕረሰሮች፣ ብረታ ብረቶች እና የተለያዩ ጨርቃ ጨርቆችና አልባሳትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የተገበረበት ንግድ ፈቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢነትና የታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ኮፒ ለጨረታው መወዳደሪያ ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ህጋዊ የንግድ ፈቃዶች እና የታክስ ከፋይነት ሰነዶችን ይጨምራል እንዲሁም ፋይናንሻል መግለጫ በፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዶቹ የድርጅታቸው ማህተምና የኃላፊው ፊርማ ያለበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኮሚቴው ሰብሳቢ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን በ7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት በኢንዱስትሪያችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጁትን ዕቃዎች በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ /አዳማ/ በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻሉ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ አዳማ ፍጥነት መንገድ የክፍያ በር መውጫ ከአዳማ ቆርቆሮ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ላይ
በስልክ ቁጥር፡- 09-10-73-78-72/ 09-39-12-50-16
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
