Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ፕሎፕ ጠጠር፣ ማስቲካ፣ የወጥ ቤት እቃ ድንኳን ሸራ እና ምስር በግልፅ እንዲሁም ጫማ፣ ኮስሞቲክስ፣ power cable and control cable እና Darmaroller 5mm በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

Kombolcha Customs Branch (የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 31/2017 ዓ.ም

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ፕሎፕ ጠጠር፣ ማስቲካ፣ የወጥ ቤት እቃ ድንኳን ሸራ እና ምስር በግልፅ እንዲሁም ጫማ፣ ኮስሞቲክስ፣ power cable and control cable እና Darmaroller 5mm በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
  2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፊኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።
  3. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሸኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  6. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው በ3፡50 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው በ4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
  8. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅፅ ቤት በስራ ሰዓት ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ እቃዎች መቶ ሺህ ብር (100,000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  11. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር፡- 033-551-06-93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender