የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠመውን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ብልሽት የገጠመውን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ፡-
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ፤ የግብር ከፋይነት ያሟላችሁና የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ሰነድ ከእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ በገ/ጉ/ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማሰራት አለባችሁ።
- የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪው ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢው በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦሪጂናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ በኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይተላለፋል።
- ወረዳው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ቢድ ቦንድ ከሆነ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
- ተሽከርካሪው የህይወት ታሪክ አለው ስለዚህ በቀጥታ የስም ዝውውር የሚደረግ ይሆናል።
- ማስታወቂያው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሚጋብዝ ቢሆንም ሌሎች ማንኛውም ፈቃድ የሌለው ግለሰብ መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 011 336 0146/ 011 336 0631
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
