በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ ፤ እና እንጦጦ ጫንጮ ዲስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/BA-06/2017
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ ፤ እና እንጦጦ ጫንጮ ዲስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ማህበራትና ድርጅቱ በጋራ የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም
- የጊንድላ፣ የአጣና፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ/ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ፡-
- ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታተይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ለ10 ተከታተይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው የጨረታ ሳጥን የሚዘጋጀው ፤ የሚታሸገው እና የሚከፈተው በሞጆ ከተማ በምስራቅ ሸዋ ዲስትሪክት ቅ/ጽ/ቤት ነው።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 0111240249 መደወል ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
