Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline26 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-26 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Vehicle Battery , Vehicle tire , Used Items

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ላይ በኮርፖሬሽኑና በተሽ/አስ/ጥ/ ዘርፍ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ ላይ በኮርፖሬሽኑና በተሽ/አስ/ጥ/ ዘርፍ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁጥር

የዕቃው አይነት

1

የከባድ ተሽከርካሪ ያገለገሉ ጎማዎች፤

2

የአነስተኛ / የቀላል ተሽከርካሪ ፤ የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች

3

ያገለገለ የመዳብ ሽቦ፤

4

የከባድና የቀላል ተሽከርካሪ ያገለገሉ ባትሪዎች፤

5

ያገለገሉ ባዶ በርሜሎች ናቸው

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ግቢ እና በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ በመቅረብ ተዘዋውረው በመመልከት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 02 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡

ጨረታውም በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣይ 8፡00 ሰዓት ላይ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡

ሐ) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጨረታ መወዳደሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

መ) ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት (የቃሊቲ ባቡር የመጨረሻ ጣቢያ ፊት ለፊት) አዋሽ ባንክ ያለበት ህንፃ በስተጀርባ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ያለበት ህንፃ ግቢ ውስጥ የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12

ስልክ ቁጥር ፡- 0114-43-20-18፣ 011-442-56-29፣

                   011-470-84-70፣ 0114-42-56-37

 

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender