Tender Detail

Tender Details

  • Company Lion Insurance Company S.C (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና አንበሳ ኢንሹራንስ ህንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-352283
  • Websitehttps://www.anbessainsurance.com/
  • Deadline20 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-21 00:00:00
  • Categories Vehicle , Vehicle Battery , Used Items

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የኩባንያው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን /የተለወጡ/ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Lion Insurance Company S.C (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)


 

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)

LION INSURANCE COMPANY (S.C.)

 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) በግጭትና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችን እና የኩባንያው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን /የተለወጡ/ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
  2. የመኪኖቹን/የንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆያ ቦታ (ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል) በስራ ሰዓት ከሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስገቢያ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታ እስከሚያልቅበት ቀን ድረስ ከዋናው መ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾ መግዛት የሚፈልጉትን የያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ካሣ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) መሆኑን እያሳወቅን ሆኖም አነስተኛ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች በማስያዣነት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ጨረታው ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ዘሪሁን ህንፃ ጎን በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ሙሉ ክፍያ በ 5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል። ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ በ10 ቀናት ንብረቶቹን ካላነሱ ለሀያ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 /መቶ ብር/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከፍለው ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዘል።
  1. ለጨረታ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ዓይነት የስም ማዛወሪያ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል።
  2.  መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  3.  ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
  4.  ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
  5.  ጨረታውን በተመለከተ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
  6.  ተጫራችች ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ወደ ስማቸው ለማዞር ከተሸጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ወደ ስማቸው ማዞር ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን ኩባንያው በተሽከርካሪው ላይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር እና ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ኩባንያው ኃላፊነት እንደማይወስድ እናሳውቃለን።
  7.  ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-352283 ወይም 0116-187000/6632947 በመደወል ወይም በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።

 

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

 

Save Tender